
የፎቶው ባለመብት, Reuters
የምስሉ መግለጫ, ከሳዑዲ ነዳጅ ማጣሪያ ሠራተኞች ለቀው እንዲወጡ ተደርገዋልኢራን
በኳታር እና በሳዑዲ አረቢያ የነዳጅ ማምረቻ ተቋማት የሰነዘረቻቸው ጥቃቶች በምርት ላይ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል በሚል ስጋት በአውሮፓ
ውስጥ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መታየቱ ተዘገበ።
የኳታር
መንግሥት ንብረት በሆነው የኤልፒጂ ጋዝ ማምረቻ ‘ኳታርኢነርጂ’ የተወሰኑ ክፍሎቹ ላይ ኢራን በሰነዘረችው ጥቃት ሳቢያ ምርት መቆሙን
አስታውቋል።
የባሕረ
ሰላጤዋ አገር ኳታር በተፈጥሮ ጋዝ ምርቷ በዓለም ላይ ቀዳሚ ከሆኑት ከአሜሪካ፣ ከአውስትራሊያ እና ከሩሲያ ጋር የምትጠቀስ አገር
ናት።
በኳታር
የጋዝ ማረምቻ ላይ ጥቃት መፈጸሙ ከተሰማ ከአጭር ጊዜ በኋላ በአውሮፓ ውስጥ የተፈጥሮ ጋዝ ዋጋ ላይ 50 በመቶ ጭማሪ ታይቷል።
በተመሳሳይ
የሳዑዲ አረቢያ መከከላያ ሚኒስቴርን ጠቅሶ የአገሪቱ ዜና ወኪል እንደዘገበው ዛሬ ሰኞ ጠዋት ሁለት ድሮኖች ራስ ታኑራ በተባለው
የነዳጅ ማጣሪያ ላይ “ጥቃት ለመፈጸም ሙከራ” አድርገዋል። ድሮኖቹን ለማክሸፍ በተደረገው ሙከራ “ትንሽ” እሳት መነሳቱም ተነግሯል።
ጥቃት
የተሰነዘረበት ነዳጅ ማጣሪያ በዓለም ትልቅ ከሆኑት ማጣሪያዎች መካከል አንዱ ሲሆን በቀን 550 ሺህ በርሜል ነዳጅ የማጣራት አቅም
አለው።
ይህ
የነዳጅ ማጣሪያ በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ካሉት ትልቁ ሲሆን፣ ለሳዑዲ አረቢያ ነዳጅ ምርት ተቀዳሚው ተጠቃሽ ማዕከል ነው።
ይህ
በኳታር እና በሳዑዲ የነዳጅ ማምረቻ ተቋማት ላይ ጥቃት የተሰነዘረው መርከቦች የዓለም አንድ አምስተኛው ነዳጅ እና አብዛኛው የኳታር
የተፈጥሮ ጋዝ በሚተላለፍበት የሆርሙዝ ሰርጥ ጥቃት ይፈጸማል በማለት መርከቦች በቆሙበት ጊዜ ነው።
የባሕር
ላይ እንቅስቃሴ መስተጓጎል፣ በነዳጅ ተቋማት ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እና ጦርነቱ ሊራዘም ይችላል የሚለው ስጋት በዓለም የነዳጅ ዋጋ
ላይ ከፍተኛ ጭማሪ አስከትሏል።