“አሁን ከአሜሪካ ጋር መደራደር ውጤታማነቱ አጠራጣሪ ነው”- ኢራን

የፎቶው ባለመብት, EPA
በተባበሩት መንግሥታት የኢራን አምባሳደር የሆኑት አሊ ባህሬኒ፤ ከአሜሪካ ጋር አሁን ላይ ድርድር ማድረግ “ውጤታማነቱ አጠራጣሪ ነው” አሉ።
ቀደም ሲል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ የኢራን ባለሥልጣናት ከአሜሪካ ጋር የመነጋገር ፍላጎት እንዳላቸው፤ ነገር ግን ጊዜው እንዳለፈባቸው እንደነገሯቸው ገልጸዋል።
የኢራኑ አምባሳደር በበኩላቸው “ከአሜሪካ ጋር ድርድር ማድረግ ውጤታማነቱ ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬ አለን” ማለታቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት የኢራን ወሳኝ ተቋማት እና መሪዎች መመታታቸውን ጠቅሰው “ለንግግር ጊዜው አልፏል” ማለታቸው ይታወሳል።
አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጦርነት መክፈታቸውን ተከትሎ ኢራን የአጸፋ እርምጃ መውሰዷን ቀጥላለች።
የኢራን እስላማዊው አብዮታዊ ዘብ ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄነራል አሊሞሐማድ ናኢም፤ በአሜሪካ እና በእስራኤል ላይ “የሲኦል በሮች ይከፈታሉ” ብለው ዝተዋል።

















