ኦስትራዊው እግር ኳስ ተጫዋች ፈጣኗን ጎል በማስቆጠር ክብረ-ወሰን ሰበረ

ኦስትራዊው እግር ኳስ ተጫዋች ክሪስቶፍ ቦምጋርትነር ጨዋታው በተጀመረ በስድስተኛው ሰከንድ ኳስን ከመረብ አገናኝቶ ፈጣኗን ጎል በማስቆጠር ክብረ-ወሰን ጨበጠ።

ስሎቫኪያ በብራቲስላቫ ኦስትሪያን አስተናግዳ 2-0 ተሸንፋለች።

የ24 ዓመቱ አማካይ ጨዋታው እንደተጀመረ ሦስት ተጫዋቾችን አልፎ ወደ ጎል የሰነዘራት ኳስ ግብ ጠባቂው ማርቲን ደብራቭካን አልፋ መረብ ላይ አርፋለች።

የክሪስቶፍ ጎል በአውሮፓውያኑ 2013 ጀመርናዊው ሉካስ ፖዶልስኪ ኤኳዶር ላይ ካስቆጠረው ጎል በአንደ ሰከንድ የፈጠነ ነው።

አንድሪያስ ዌይማን ሁለተኛውን ጎል አክሎ የራልፍ ራኚክ ቡድን ደል እንዲቀዳጅ አድርጓል።

ቅዳሜ ምሽት በተደረገ ሌላ የወዳጅነት ጨዋታ ፈረንሳይ ከጀመርን ተገናኝተው ጀርመናዊው ፍሎሪያን ሪትዝ ጨዋታው በተጀመረ በ7ኛው ሰከንድ ከርቀት የመታት ኳስ በፈረንሳዩ ተከላካይ ኡፔሜካኖ ተጨርፋ ጎል ሆናለች።

ማክሰኞ በቪዬና ቱርክን የምታስተናግደው ኦስትሪያ አራት ተከታታይ ጨዋታዎች በማሸነፍ ጀመርን ለምታስተናግደው የዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ዝግጅቷን አያጠናከረች ነው።

ለአርቢ ሊፕዚግ የሚጫወተው ቦማጋርትነር ፊሽካው ከተነፋ ከስድስተኛው ሰከንድ ላይ ያስቆጠራት ጎል የስሎቫኪያ ደጋፊዎችን ያስደነገጠች ነበረች።

በአውሮፓውያኑ 1993 እንግሊዝ ከሳን ማሪኖ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሲጫወቱ ዴቪድ ጉዋልቲዬሪ በስምንተኛው ሰከንድ ለሳን ማሪኖ ማስቆጠሩ ይታወሳል።

በተመሳሳይ ቤልጂየማዊው ክሪስቲያን ቤንቴኬ ጂብራልታር ላይ በ2017 በስምንተኛው ሰከንድ ጎል አስቆጥሯል።

በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ፈጣኗ ጎል በ2019 የሳውዝአምፕተኑ ሼን ሎንግ ጨዋታው በተጀመረ በ7.69 ሰከንድ ዋትፈርድ ላይ ያስቆጠራት ናት።

ቅዳሜ በተደረጉ የወዳጅነት ጨዋታዎች እንግሊዝ በዌምብሊ ስታድየም በብራዚል 1-0 ተረትታለች።

ፈረንሳይ በሜዳዋ በጀርመን 2-0 ስትረታ፤ አርጀንቲና ኤል-ሳልቫዶርን 3-0፣ ቱኒዚያ ደግሞ ክሮሺያን በፍፁም ቅጣት ምት 5-4 አሸንፋለች።