ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
BBC News, አማርኛ - ዜና
ቀጥታ, የአሜሪካ ባሕር ኃይል የኢራን ጦር መርከብን በሚሳዔል መትቶ ሲያሰምጥ ቢያንስ የ80 ሰዎች ሕይወት አለፈ
የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ፔት ሄግሴት የአሜሪካ ጦር ኃይል በሕንድ ውቅያኖስ ላይ አንድ “የኢራን የጦር መርከብ” በውሃ ውስጥ የሚምዘገዘግ ሚሳዔል በመጠቀም ማስመጡን ተናግረዋል። በኢራን የጦር መርከብ ላይ የነበሩ 80 ሰዎች አስከሬን መገኘቱን ደግሞ የሲሪላንካ መከላከያ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ማርሻል ሳምፓዝ ቱያኮንታ ለቢቢሲ ሲንሃላ ተናግረዋል።
ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ የህወሓት አመራር "ሰፊ ወታደራዊ ዝግጅት" እያደረገ ነው አሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ የህወሓት አመራር "ሰፊ ወታደራዊ ዝግጅት"፣ "የጦር መሣሪያ ግዥ" እና "ወታደራዊ ቅስቀሳዎችን እያደረገ ነው" ሲሉ በትግርኛ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ከሰሱ። በፌደራል መንግሥት በኩል "በጭራሽ ትግራይ ላይ የሚጀመር ጦርነት እንደሌለ" አረጋግጣለሁ ሲሉም ተናግረዋል።
አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት፡ ዋና ዋና እውነታዎች በካርታ
አሜሪካ እና እስራኤል በፈጸሙት ጥቃት የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ሲገደሉ፤ ኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ላይ ጥቃት መፈጸም ቀጥላለች። እየተካሄደ ስላላው ጦርነት፣ ስለ ኢራን እና ባለፉት ቀናት ስለተከሰቱ ዋና ዋና ነገሮች ሊያውቋቸው የሚገቡ እውነታዎች በምሥል እዚህ ይመልከቱ።
ሱዳን ከኢትዮጵያ የሚነሱ ድሮኖች ድንበሯን ጥሰው እየገቡ መሆናቸውን በመግለጽ ከሰሰች
ሱዳን ከኢትዮጵያ የሚነሱ ድሮኖች ወደ ግዛቷ ዘልቀው በመግባት ጥቃት እየፈጸሙ መሆኑን እና ይህም በሉዓላዊነቷ ላይ የተፈጸመ "ግልጽ ጥሰት" እንዲሁም "የጠብ ጫሪነት ድርጊት" ነው ስትል ከሰሰች። ቢቢሲ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቀረበው ክስ ላይ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም።
በአርሲ ዞን ባለፈው ሳምንት ውስጥ ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች ተናገሩ
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ባለፈው ሳምንት ውስጥ ታጣቂዎች በፈጸሟቸው ጥቃቶች ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች እና የቤተ ክርስቲያን ኃላፊዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። እሁድ ምሽት በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ ሁለት ሰዎች እንደተገደሉ ሦስት የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች
ቪዲዮ, የአራኑ ኃያል ሰው አያቶላህ ኻሜኒ ማን ናቸው? ሥልጣናቸውስ ምን ያክል ጠንካራ ነው?
ኃያሉ የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ እስራኤል እና አሜሪካ በቅንጅት በፈጸሙት ጥቃት መገደላቸው ተረጋግጧል። ከ35 ዓመታት በላይ ኢራንን የመሩት ኻሜኒ በእስላማዊ ሪፐብሊኳ ኢራን መንግሥት ውስጥ የነበራቸው ሚና እጅግ የጎላ ነበር። ጠቅላይ መሪው ከየት ተነስተው ምዕራባውያን በተለይ የአሜሪካ እና የእስራኤል ዒላማ አስከመሆን ደረሱ?
ቪዲዮ, ቱርክን ወደ ኦቶማን ዘመን ዝናዋ ለመመለስ የሚጥሩት ኤርዶዋን ምን እያደረጉ ነው?
ቱርክ ከኦቶማን ግዛተ መንግሥት መውደቅ በኋላ እንደ አገረ መንግሥት ከተመሠረተች 100 ዓመታት አለፋት። የቱርክ አባት በመባል የሚታወቁት አታቱርክ፣ አገራቸውን ከሃይማኖት ገለልተኛ እና ዘመናዊ እሳቤን እንድትላበስ መሠረት ጥለዋል። በዘመናዊው ዓለም መድረክ ጉልህ ተጽዕኖ ያላቸው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን እንደ ኦቶማን ዘመን ሁሉ ቱርክን በዓለም ኃያል ለማድረግ እየጣሩ ነው። ይሳካላቸው ይሆን?
ቪዲዮ, ኢትዮጵያ የባሕር በር “በባሌም ሆነ በቦሌ ማግኘቷ አይቀርም”- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር መንግሥታቸው ከኤርትራ ጋር ስለገባበት ቅራኔ አጀማመር ከዚህ በፊት ያልተናገሩትን ጉዳይ እማኞችን ጠቅሰው ተናግረዋል። በተጨማሪም በሁለቱ አገራት መካከል ለተፈጠረው መቃቃር ሌላ ምክንያት የሆነው የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ፍላጎት “በባሌም ሆነ በቦሌ” የሚሳካ ነው በማለት በአርግጠኝነት ነው ተናግረዋል።
ቪዲዮ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስለሕዳሴ ግድብ እስካሁን ምን አሉ?
ከቀናት በፊት በአባይ (ናይል) ጉዳይ ኢትዮጵያ እና ግብፅን ለማደራደር ጥያቄ ያቀረቡት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ኢትዮጵያ የናይል ወንዝ "ፍሰትን የሚያስቆም ግድብ" ሠርታለች አሉ። በዚህም ምክንያት ግብፅ ከናይል ወንዝ "በቂ ውሃ እንደማታገኝ" የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህንን ጉዳይ "መፍታት ይኖርብኛል" ሲሉ ተደምጠዋል። ለመሆኑ ፕሬዝዳንቱ በተለያዩ ወቅቶች በጉዳዩ ዙሪያ ምን ተናገሩ?
ቪዲዮ, የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ምን ማለት ይሆን?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ አቅራቢያ 'አቡሴራ' በተባለ አካባቢ የሚገነባው አዲስ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ቅዳሜ ጥር 2/2018 ዓ.ም. መሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል። 12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚወጣበት የአውሮፕላን ማረፊያ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ሲጠናቀቅ፣ በዓመት 60 ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገድ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። 3,500 ሔክታር መሬት የሚሸፍነው ይህ ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ አውሮፕላን ማረፊያ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ በዓመት 110 ሚሊዮን መንገደኞችን ያስተናግዳል ተብሏል።
ቪዲዮ, ከፍተኛ የነዳጅ ሀብት ያላት አሜሪካ ለምንድን ነው በሌሎች አገራት ነዳጅ ላይ ዐይኗን የጣለችው?
አሜሪካ ከፍተኛ የነዳጅ ክምችት ቢኖረትም በሌሎች አገራት ውስጥ ባሉ የነዳጅ ክምችቶች ላይ ዘወትር ትረኩት ደታርጋለች። ለዚህ በበርካታ አገሮች ጦርነት ውስጥ በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ ስትሳተፍ ቆይታለች። በቅርቡም በቬንዙዌላ ሰጥ ቀጥተኛ ወታደራዊ እርምጃ በመውሰድ መሪዋን ይዛ ወስዳለች። ከዚያም በኋላ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቬንዙዌላ የነዳጅ ሀብት ላይ አሜሪካ ያላትን ፍላጎት በይፋ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ተደምጠዋል።
ቪዲዮ, “ጦርነትን በተግባር እናውቀዋለን” ፕሬዝዳንት ኢሳያስ
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከአገራቸው ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ላለው ውጥረት እና ለተፈጠረው ችግር ከጀርባ ሆኖ የሚገፋ ወገን እንዳለ ተናግረዋል። ጦርነት ሊከሰት የሚችልበት እድል እንዳለ የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ ለዚህም ዝግጁ መሆናቸውን በመግለጽ “ጦርነትን በተግባር እናውቀዋለን” ብለዋል።
ቪዲዮ, አሜሪካ ዐይኗን የጣለችው በማዱሮ ላይ ወይስ በቬንዙዌላ ነዳጅ ላይ?
አሜሪካ ማዱሮ ላይ በዕጽ እና በጦር መሳሪያ ዝውውር ብትከሳቸውም ዋነኛ ትኩረቷ ቬንዙዌላ ባላት የተትረፈተፈ የነዳጅ ሀብት ላይ እንደሆነ ይነገራል። ትራምፕም ይህንን ሳይደብቁ ተገቢው ሽግግር እስኪደረግ ድረስ ቬንዙዌላ በአሜሪካ እንደምትመራ እና ኩባንያዎቿ የነዳጅ ምርት ሥራውን እንደሚረከቡ በግልጽ ተናግረዋል።
ቪዲዮ, የሶማሊላንድ ቀጣዩ ዕውቅና የማግኘት ፈተና፡ ቀጥሎ ማን ዕውቅና ይሰጣታል?
እስራኤል ለሶማሊላንድ አገርነት ይፋ ዕውቅና መስጠቷን ተከትሎ የሶማሊላንድ እና የሶማሊያ እንዲሁም የቀጣናው ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል የሚለው ጥያቄ መነሳት ጀምሯል።
ቪዲዮ, ይህ የኢትዮ ጃዝ ፈጣሪው ሙላቱ አስታጥቄ የመጨረሻ የሙዚቃ ሥራው ይሆን?
የሙላቱ የሙዚቃ ጉዞ አስርት ዓመታትን ያስቆጠረ ነው። የተወለደው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያዋ ከተማ ጅማ ነው። ነገር ግን ለዩናይትድ ኪንግደም ትልቅ ቦታ አለው። ትምህርቱን በዌልስ ነው የተከታተለው። ሙላቱ ወደ ሙዚቃው ዓለም እንዴት ገባ? ከዚህ በኋላስ መድረክ ላይ እናየው ይሆን?
አነጋጋሪ ጉዳይ
ኤምሬቶች፣ ቱርክ እና ሳዑዲ ከኢትዮጵያ የሚፈልጉት ምንድን ነው?
የኢትዮጵያ ስም ከተገዳዳሪዎቹ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ከሳዑዲ አረቢያ ጋር ተያይዞ መነሳት ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል። ለመሆኑ የባሕረ ሰላጤው አገራት ከንግድ እና ኢንቨስትመንት ጀርባ ያሉ ፖለቲካዊ ፍላጎቶቻቸው ምንድን ናቸው? የኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ ወዳጅ የሆነችው ቱርክ ያላት ሚናስ ምንድን ነው?
ባላንጣዎቹ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የፍልሚያ ሜዳ ያደረጉት የአፍሪካ ቀንድ
በባላንጣነት የሚታየዩት የመካከለኛው ምሥራቅ ኃያላን ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ወታደራዊ ለውጦች እንዲታዩ ምክንያት እየሆኑ ነው። በተለይ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ሱዳን የእነዚህ አገራት ዋነኛ የመፎካከሪያ መድረኮች ሆነዋል። በተጨማሪም ቱርክ በቀጣናው ያላት ሚና እየጎላ ነው። ይህ ፉክክር ለአፍሪካ ቀንድ ምን ይዞ ይመጣል?
ጥንታዊቷን ደብረ ታቦር ከተማ ለዓመታት ወደኋላ መልሷታል የተባለው ያልተነገረው ውድመት
በአማራ ክልል ውስጥ በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት ከተቀሰቀሰ ከሐምሌ 2015 ዓ. ም. ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ የመንግሥት ተቋማት ውድመት በደብረ ታቦር ከተማ ደርሷል። በክልሉ ባለፉት ዓመታት የንፁሃን ግድያን ጨምሮ ንብረቶች መውደማቸውን የተለያዩ ሪፖርቶች ያመላከቱ ሲሆን፤ ግጭቱ ከተቀሰቀሰ ወዲህ በከተሞች ላይ ግን ሰፊ ውድመት ሲደርስ የደብረ ታቦር የተቋማት ውድመት የመጀመሪያው ነው።
"የአማራ ክልል 95 በመቶ አካባቢ ሰላም ነው" ጋሻው መርሻ የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
በአማራ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ እና ስለፓርቲው ማብራሪያ እንዲሰጡ ቢቢሲ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ከሆኑት ከአቶ ጋሻው መርሻ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል። አቶ ጋሻው በአገራዊ፣ በክልላዊ እና በአብን ጉዳዮች ላይ የቀረቡላቸውን ጥያቄ ከሞላ ጎደል ከመለሱ በኋላ ቢቢሲን በወገንተኝነት በመክሰስ ቃለ ምልልሱን አቋርጠዋል። ቃለ ምልልሱን እንዲያቋርጡ ያደረጋቸው ጥያቄ ምን ነበር?
የወልቃይት ጠገዴ ኮሚቴ በምርጫ ቦርድ እና በስምረት ፓርቲ የፍርድ ቤት ክርክር ውስጥ ለመግባት ጠየቀ
የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአከራካሪ የምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫ እንዲያካሄድ ባሳለፈው ጊዜያዊ ዕግድ ውስጥ ገብቶ ለመከራከር አቤቱታ አቀረበ። በዚህም መሠረት ፍርድ ቤቱ ጉዳዮን ተመልክቶ ውሳኔ ለመስጠት ለየካቲት 25/2018 ዓ. ም. ቀጠሮ መስጠቱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ብራዚል. . .በዓለም አቀፍ ቱሪስቶች እንዲመረጡ ያደረጋቸው ምሥጢር ምንድን ነው?
ዓለም አቀፍ ቱሪዝም ከመቼውም በላይ እየተነቃቃ ነው። በአውሮፓውያኑ በ2025 1.5 ቢሊዮን ቱሪስቶች የተለያዩ አገራትን ጎብኝተዋል። በአገራቱ ዝርዝር ከተካተቱ መካከል ኢትዮጵያ ተጠቃሽ ናት። ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ብራዚል እና ሲሸልስ በአስጎብኚዎች እና በጎብኚዎች ተመራጭ ያደረጋቸው ምንድን ነው?
"የአፍሪካ ቀንድ የውጭ ኃይሎች የጦር ሜዳ መሆን የለበትም" - የቱርክ ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን
ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን አገራቸው በአፍሪካ ቀንድ "አዲስ ግጭቶች እና ሕመም መመልከት" እንደማትፈልግ እንዲሁም ቀጣናው "የውጭ ኃይሎች የጦር ሜዳ" መሆን እንደሌለበት ተናገሩ። የቱርኩ ፕሬዝዳንት አክለውም፤ እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችው የአገርነት ዕውቅና "ለሶማሊላንድም ሆነ ለአፍሪካ ቀንድ ምንም ጥቅም" አይኖረውም ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ "ኢትዮጵያ የመስፋፋት ፍላጎት የላትም" አሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የረመዳን ጾም መጀመርን በማስመልከት የካቲት 9/2018 ዓ.ም. በአረብኛ ቋንቋ ባስተላለፉት መልዕከት "ኢትዮጵያ የመስፋፋት ፍላጎት የላትም" አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዚህ መልዕክታቸው ላይ ኢትዮጵያን "የታማኝነት የእውነት ምድር" ሲሉ የጠሯት ሲሆን "የጎረቤቶቿን ደህንነት አደጋ ላይ እንደማትጥል" ተናግረዋል።
በአፍሪካ ቀንድ ሚናዋ እየጎላ የመጣው የቱርክ የሽምግልና ጥረት እና የገጠሟት እንቅፋቶች
ፕሬዝዳንቷ ለይፋዊ ጉብኝት በዚህ ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚያቀኑት ቱርክ በወሳኝ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ተሰሚነቷ እየጎላ ነው። አገሪቱ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተለያዩ አገራት መካከል ባጋጠሙ ቀውሶች ውስጥ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ትነሳለች። ለመሆኑ ቱርክ ጉልህ ሚና በነበራት ጉዳዮች ውስጥ ምን አሳካች? ምንስ እንቅፋት ገጠማት?
የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?
የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!
ከየፈርጁ
ፆም በሰውነታችን ውስጥ የሚያስከትለው ለውጥ እና የሚሰጠው ጥቅም ምንድን ነው?
ለእስልምና እና ለክርስትና እመነት ተከታዮች ዋነኞቹ የፆም ወቅት የሆኑት ረመዳን እና ዓቢይ ፆሞች ተጀምረዋል። የሁለቱም እምነቶነቶች ምዕመናን የፆሙን ጊዜ በየራሳቸው ሥርዓት እና ደንብ መሠረት የሚከውኑት ሲሆን፣ በየዕለቱ ለረጅም ሰዓታት ከምግብ እና ከውሃ ርቀው ይቆያሉ። በዚህ ጊዜ ታዲያ ፆም በሰውነት ላይ ምን ለውጥን ያስከትላል? ምንስ ጥቅም አለው?
ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ስጋት ውስጥ መኖር
ግጭቶች በሰው ሕይወት እና አካል እንዲሁም በንብረት እና በመሠረተ ልማቶች ላይ ከሚያደርሱት ጉዳት ባሻገር በሰዎች አካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ጤና እና ደኅንነት ላይ ከባድ ተጽእኖን እንደሚያስከትል ባለሙያዎች ይናገራሉ። እንዲህ ባለው ሁኔታ ውስጥ ስንሆን የሚከሰቱ ሥነ ልቦናዊ ለውጦች ምንድን ናቸው? ለመቋቋምስ ምን ማድረግ እንችላለን?
ኖስትራዳመስ፡ የፈረንሳያዊው ኮከብ ቆጣሪ ትንቢቶች ለምን አሁንም ድረስ ተቀባይነት አገኙ?
በመቶዎች ከሚቆጠሩ ዓመታት በኋላ ደጋፊዎቹ ሁለቱንም የዓለም ጦርነቶች፣ የሂሮሺማ እና የናጋሳኪ የኒውክሌር ፍንዳታዎችን፣ የሂትለርን መነሳት እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ጨምሮ ብዙ ታሪካዊ ክስተቶችን፣ ምንም እንኳን እነዚህን ክስተቶች በስም ባይጠቅሳቸውም እንደተነበየ ይናገራሉ።
የታዋቂ ሰዎችን ስም መነጋገሪያ ያደረገው የወሲብ ወንጀለኛው ጄፍሪ ኤፕስቲን ማን ነው?
የጄፍሪ ኤፕስቲን ሰነዶች ይፋ መሆናቸውን ተከትሎ በመላው ዓለም የሚገኙ ታዋቂ ግለሰቦች እና ተቋማት በአሉታዊ መልኩ ስማቸው እየተነሳ ነው። በዚህም ምክንያት ፖለቲከኞች እና ታዋቂ ሰዎች ዝናቸው ጥያቄ ውስጥ ገብቶ አንዳንዶቹም ከሥልጣን እና ከኃላፊነታቸው እየለቀቁ ነው። ለመሆኑ ለዚህ ሁሉ ቀውስ ምክንያት የሆነው ጄፍሪ ኤፕስቲን ማን ነው?
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
አጃኢብ!
ሺህ ዘመናት የተሻገረው ኩል ለጤና እና ለውበት ያለው ጥቅም
የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ተቋም በዓለም የማይዳሰሱ ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ ኩልን አካቶታል።
የእስራኤል እና የኢራን ግጭት
አደገኛው ታጣቂ ቡድን አይ ኤስ በምዕራቡ ዓለም ዳግም እየተጠናከረ ይሆን?
አይኤስ በመካከለኛው ምሥራቅ የነበረውን ድጋፍ እያጣ ከመጣ ወዲህ በአፍሪካ የተለያዩ አገራት ውስጥ እግሩን እያስገባ ነው። በምዕራብ አፍሪካ አገራት 12ሺህ የሚደርሱ ተዋጊዎች ያሉት አይኤስ በጎረቤት አገር ሶማሊያ ውስጥም ይንቀሳቀሳል። በዴሞክራቲክ ኮንጎ፣ በሞዛምቢክ እና ናይጄሪያም ቡድኑ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋል።
በቀይ ባሕር የጦር ሰፈር ለማቋቋም የተቃረበችው ሩሲያ ለቀጣናው ምን ይዛ ትመጣለች?
ከከተፎካካሪዎቿ ዘግይታ ወደ ቀይ ባሕር ወታደራዊ ኃይሏን ለማስፈር የተቃረበችው ሩሲያ በወሳኙ የባሕር መተላለፊያ ላይ ላይ አዲስ ኃይል ትሆናለች። በአፍሪካ የመጀመሪያዋን የባሕር ኃይል ጦር ሰፈር ለመመሥረት ስትጥር የቆየችው ሩሲያ አሁን ፍላጎቷን ዕውን ለማድረግ ተቃርባለች። ይህ የሩሲያ ኃይል ወደ ቀጣናው መምጣት ምን ይዞ ይመጣል?
አሜሪካ የ10 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ያቀረበችበት የዋይት ሐውስ እንግዳ፡ አህመድ አል ሻራ
አዲሱ የሶሪያ ፕሬዝዳንት አህመድ አል ሻራ በአግባቡ የተተኮሰ ሱፍ ለብሰው፣ ፀጉራቸውን ወደ ኋላ አበጥረው ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ ሲመጡ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንዳሉ ያስታውቃል። አሁን የትግል ልብሳቸውን ትተው፣ አዲስ ስም ይዘው በዓለም ላይ ካሉት በጣም ኃያላን መሪዎች ጋር ይጨባበጣሉ።
በመካከለኛው ምሥራቅ ኃያል የሆነችው የአይሁዶች አገር እስራኤል እንዴት ተመሠረተች?
በመካከለኛው ምሥራቅ ኃያል እና ብቸኛዋ የአይሁዶች አገር የሆነችው እስራኤል በዙሪያዋ ካሉ አገራት ሁሉ በዕድሜ ትንሿ ናት። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቃት በኋላ በአውሮፓውያኑ 1948 የእስራኤል እንደ አገር መመሥረት በአካባቢው አሁን ድረስ እየተካሄደ ያለ ለውጥን አስከትሏል። ለመሆኑ በየዕለቱ የዓለም መገናኛ ብዙኃን ስሟን ሳያነሱ የማያልፏት ይህች አገር እንዴት ተመሠረተች?
እስራኤል 15 የጦር አውሮፕላኖችን አሰማርታ ኳታር ውስጥ የፈጸመችው ጥቃት
በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ውስጥ እስራኤል ጥቃት የፈጸመችው በርካታ የሐማስ ፖለቲካ ቢሮ ባለሥልጣናት በሚኖሩበት የመኖሪያ አካባቢ ላይ ነው። በዚህ ጥቃት አስከ ስምንት የሚደርሱ ፍንዳታዎችን እና ከፍተኛ ጭስ በዶሃ ሰሜናዊ ክፍል ላይ ማየታቸውን ዓይን እማኞች ተናግረዋል። ከጥቃቱ ደቂቃዎች በኋላ ደግሞ እስራኤል ለተፈጸመው ጥቃት በይፋ ኃላፊነቱን ወስዳለች።
የእስራኤል ፕሬዝዳንት እንዲሆን ተጠይቆ የነበረው ታዋቂው የፊዚክስ ሊቅ አልበርት አንስታይን
የጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ቤን ጉርዮን መንግሥት በዓለም ታዋቂ የሆነው ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን ለእስራኤል ፕሬዝዳንትነት እንዲሆን ካጩት በኋላ በዩናይትድ ስቴትስ የእስራኤል አምባሳደር አባ ኢባን አንስታይንን እንዲያነጋግሩ ተደረገ።
የተመለሱ ጥያቄዎች
"ተወዳጇ እና ደስተኛዋ ልጄ እንዴት በራሷ ላይ ወሰነች?" - በቲክ ቶክ እና በእኩዮቿ ጫና ራሷን ያጠፋቸው ኢትዮጵያዊት ታዳጊ
አቶ ነብዩ ማኅበራዊ ሚዲያ በታዳጊ ልጆች ላይ የሚያስከትለውን ተጽእኖ በተመለከተ መራራ የሆነ ልምድ ነው ያላቸው። የ13 ዓመቷ ልጃቸው ፊዮሬላ ላይ ምንም ዓይነት ምልክት ሳይመለከቱ በእኩዮቿ ጫና እና በማኅበራዊ ሚዲያ ግፊት ባላሰቡት ጊዜ ልጃቸው እራሷን አጥፍታ አግኝተዋታል።
አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ ቢሾፍቱ እንዲሆን ለምን ተመረጠ?
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ግዙፍ የሚባለው የአውሮፕላን ማረፊያ ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ያህል በሚርቅ ቦታ ላይ ለመገንባት ሥራ ጀምራለች። ይህ አውሮፕላን ማረፊያ መሃል አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኘው በብዙ እጥፍ የሚበልጡ መንገደኞችን ያስተናግዳል ተብሏል። ይህንን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ለምን አሁን መገንባት አስፈለገ? ቦታውስ ለምን ተመረጠ?
ሌላ ዕይታ
ቢቢሲ አማርኛን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉ
ከማኅደራችን
ማርበርግ ቫይረስ: የመጀመሪያው ታማሚ እና ሦስት መሪዎቿን ያጣችው የጂንካ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን
ከሌሊት ወፎች የሚነሳው የማርበርግ ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተገኘ አንድ ወር ሊደፍን ጥቂት ቀናት ቀርተውታል። የጤና ሚኒስቴር፤ እንዴት በሽታው በጂንካ ከተማ ሊነሳ እንደቻለ እስካሁን አልገለጸም። ለመሆኑ በጂንካ የመጀመሪያው ታማሚ ማን ነበር? የበሽታው መነሻ የሆኑት የሌሊት ወፎችን እና የመጀመሪያውን ታማሚስ ምን አገናኛቸው? ቢቢሲ ባደረጋቸው በርካታ ቃለ መጠይቆች ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ የሚሆኑ መረጃዎች አሰባስቧል።
"ቢገድሉኝ ይሻል ነበር"፡ የሴቶችን ሕይወት እያበላሸ ያለው የተዘነጋው የአማራ ክልል ጦርነት
ከሁለት ዓመት በላይ የሆነው በአማራ ክልል በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በሚካሄደው ግጭት ሰላማዊ ሰዎች ከባድ ዋጋ እየከፈሉ ነው። ግጭቱ በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት ባሻገር በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እና ሰቆቃ ትኩረትን አላገኘም። ቢቢሲ ለወራት ባካሄደው ክትትል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴቶች የመደፈር እና የወሲባዊ ጥቃት ሰለባ መሆናቸውን መረጃ አግኝቷል።
በብርሌ ፍቅር የወደቁት ፈረንጅ 'ብርሌ ውስጥ የኢትዮጵያ ታሪክ አለ' ይላሉ
ሰሞኑን አረቄ ብሔራዊ አጀንዳ ሆና የማኅበራዊ ሚዲያ አናት ላይ ወጥታ ነበር። ጠጅ ቢሆን አናት ላይ አይወጣም፤ ወደ ጉልበት ነው የሚወርደው። ጠጅ ለመጨረሻ ጊዜ ጉዳይ ሆኖ የሥነ መንግሥቱ አናት ላይ ወጥቶ፣ 'ብሔራዊ አጀንዳ' የነበረው በዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ዘመን ነው። ድሮ ጠጅ በብርሌ ይቀርብ ነበር። ከዚያ በብርሌ ይጠጣ ጀመር። ጠጅ ግን እንደ አረቄ ማንም ‘ተራ ዜጋ’ ብድግ አድርጎ አያንደቀድቀውም።ብርሌ ውስጥ የመደብ ታሪክ አለ። የዘመን ታሪክ አለ። የጭሰኛና የመሳፍንት ታሪክ አለ። ያልተሳከረ።
ዓለምን የሚዞረው ኢትዮጵያዊ ከዩቲዩብ ምን ያህል ያገኛል?
ከተከፈተ በዚህ ወር 20 ዓመት የሆነው የቪዲዮ ማጋሪያው የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ ዩቲዩብ ለብዙዎች የተለያዩ አጋጣሚዎችን ፈጥሯል። ከእነዚህም መካከል አቤል ብርሃኑ አንዱ ነው፤ በዩቲዩብ አማካኝነት 62 ሀገራትን ዟሯል። ያልረገጠው አህጉር አንታርቲካን ብቻ ነው። ሁሉንም የአሜሪካ ግዛቶች አካሏል። ከዘጠኝ ዓመታት በላይ ዩቲዩብ ላይ የቆየው አቤል ከዩቲዩብ ምንያህል ያገኛል?
ቪዲዮ, በአርሰናል ‘ፍቅር የወደቁት’ የ65 ዓመቷ እናት፡ ወይዘሮ እቴቱ ማሞ, ርዝመት 3,29
ከእንግሊዝ ታላላቅ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የአርሰናል የልብ ደጋፊ የሆኑት ወ/ሮ እቴቱ ማሞ የ65 ዓመት እናት ናቸው። ላለፉት 20 ዓመታት አርሰናልን ያለማቋረጥ ደግፈዋል። እንደብዙዎቹ የቡድኑ ደጋፊዎች ዘንድሮ አርሰናል ዋንጫ ባለማንሳቱ ቢከፉም ድጋፋቸው ግን እንደሚቀጥል ይናገራሉ። ከሁሉም ተጫዋቾች ይልቅ እሳቸው ገብረኢየሱ ለሚሉት ለጋብሬል ጀሱስ እና ለቡካዮ ሳካ የተለየ ፍቅር አላቸው።
እነ ሞገስ አስገዶም፣ አብረሃ ደቦጭ፣ ፕ/ር አስራት ወልደየስ፣ ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም፣ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር የተማሩበት ተፈሪ መኰንን
ተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት ታሪክ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ንድፍ እንደማለት ነው። ላለፉት 100 ዓመታት ታላላቅ ሰዎችን ወልዷል። ለመኾኑ ይህ ተማሪ ቤት እነማንን አፈራ? ይህ ሐተታ በ100 ዓመት ታሪኩ ውስጥ በአንድም ሆነ በሌላ አሻራቸውን ያሳረፉትን ግለሰቦች ያወሳል፤ ከካናዳዊያን ጄስዊቶች እስከ ከንቲባ አዳነች አበቤ፤ ከቱጃሩ ራስ ኃይሉ ተክለሃይማኖት እስከ ቢሊየነሩ ሼክ አላሙዲን፣ ከሐኪም ወርቅነህ እሸቴ እስከ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ።
ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት የምትገኘው አሊ ዶሮ እና አካባቢዋ ለምን የእገታ ማዕከል ሆኑ?
ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በሕዝብ እና በጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እና እገታዎች ተበራክተዋል። ይህ ክስተት ደግሞ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው የሰሜን ሸዋ አካባቢ በተደጋጋሚ ሲከሰት ቆይቷል። በተለይ አሊ ዶሮ የሚባለው ቦታ የጥቃት እና የእገታ ማዕከል ሆኗል እየተባለ ነው። ቢቢሲ በተለይ ይህ ቦታ ለምን የመንገደኞች እና የአሽከርካሪዎች ‘የሞት ቀጣና’ ሆነ? በሚል ለወራት የዘለቀ ምርመራ አድርጓል።
ባይተዋር ከተማ፡ “ፒያሳ፣ ካዛንቺስ... ሰፈሬ አልመስል አሉኝ”
ባለፉት ዓመታት በአዲስ አበባ በቅርስነት ተመዝግበው የነበሩ እንዲሁም ሌሎችም ታሪካዊ ሕንጻዎች፣ ቤቶች እና አካባቢዎች እንደ ዋዛ አፈር ለብሰዋል። በዚህ ዘገባ፣ አንድን ሕንጻ ወይም ቤት ቅርስ አልያም ታሪካዊ ሥፍራ ለማለት መስፈርቱ ምንድን ነው? የታሪካዊ ሕንጻዎች እና ቤቶች መፍረስ በታሪክ፣ በነዋሪዎች ሥነ ልቦና፣ በኪነ ሕንጻ እና በማኅበራዊ መስተጋብር ላይ ምን ጫና ያሳድራል? ቅርሶች እና ታሪካዊ ሥፍራዎችን እንዴት ጠብቆ ማደስ፣ ማዘመን፣ መልሰው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ እንዲሁም ከሌሎች ግንባታዎች ጋር ጎን ለጎን እንዲሄዱ ማድረግ ይቻላል? የሚሉት እና ተያያዥ ነጥቦች ተዳስሰዋል።
“ሰው መሃል ሆኜ ሁሉም ጨካኝ ሆኖብኝ ነበር” - የፀጋ በላቸው ዘጠኝ የጠለፋ ቀናት
ግንቦት 2015 ዓ.ም. የተፈጸመው የፀጋ በላቸው ጠለፋ ብዙዎችን ያስቆጣ፣ መነጋገሪያም የሆነ የወንጀል ድርጊት ነበር። ፀጋ፤ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት ተጠልፋ ያሳለፈቻቸውን ቀናት በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቢቢሲ በዝርዝር ተናግራለች። ከቢቢሲ ጋር በነበራት ዘለግ ያለ ቆይታ፤ ስለተጠለፈችበት መንገድ እና ስላሳለፈቻቸው ዘጠኝ ቀናት በዝርዝር ተርካለች። ከጠለፋው ነጻ የወጣችበት መንገድም አስቀድሞ በክልሉ መንግሥት ከተገለጸው የተለየ እንደሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግራለች። ለምን ከኢትዮጵያ እንደተሰደደች እና ስለ ቀጣይ ዕቅዶቿም እንዲሁ አጋርታለች።
". . . ከምድሩ ይልቅ የሰማዩን መንገድ ለመምረጥ ተገደናል" እገታ ያሰጋቸው መንገደኞች
ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ የሚካሄዱ ግጭቶች እና በታጣቂዎች የሚፈጸሙ እገታዎች ዜጎች በፈለጉት ጊዜ እና መንገድ በአገሪቱ ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ ብርቱ ስጋት ፈጥሮባቸዋል። በተለይ ደግሞ የመንገደኞች ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን በማድረግ የሚፈጸሙት ያላባሩ እገታዎች በዋነኞቹ የአገሪቱ ክልሎች ውስጥ እንቅስቃሴን አዳጋች አድርገውታል። በዚህም ሳቢያ አቅሙ ያላቸው እና የግድ የሆነባቸው ሰዎች ፊታዎችን ወደ አየር ትራንስፖርት አዙረዋል።
"'ቁርጭምጭሚት' የሚለው ቃል ያስቀኛል'' ለ23 ዓመታት ለፈረንጆች አማርኛን ያስተማረችው ፖላንዳዊት፣ ዶ/ር ኤቫ ቮልክ-ሶሬ
ፓላንዳዊቷ ዶ/ር ኤቫን የአማርኛ ቋንቋን ከ40 ዓመት በፊት ተምራ በዲግሪ ከተመረቀች በኋላ ከሃያ ዓመታት በላይ በማስተማር በርካቶችን በአማርኛ ቋንቋ ዲግሪ አስይዛለች። የምታስተምርበት ዩኒቨርስቲ ወደ 80 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አማርኛን እያስተማረ ነው። አማርኛ ቋንቋን “ፏፏቴ ነው” የምትለው ዶ/ር ኤቫን በአገሯ በአማርኛ አስተርጓሚነት ትሠራለች። ለመሆኑ እንዴት ከአማርኛ ጋር ተዋወቀች?
"ብልጽግናዎች ይዘውን እንዲጠፉ አንፈቅድም፤ አገራችን ሕዝባችን ነው፤ ዝም አንላቸውም" - ጃዋር መሐመድ
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ካላቸው ፖለቲከኞች መካከል ጃዋር መሃመድ አንዱ ነው። ለዓመታት ያህል በኦሮሚያ የነበሩ ትግሎችን እንዲሁም ተቃውሞዎችን ከጀርባም ሆነ ከፊት ሆኖ በማስተባበር እና በመምራት ግንባር ቀደም ነው።የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ አመራሩ ጃዋር ከትውልድ አንስቶ በፖለቲካ ህይወቱ የተጓዘበትን ህይወቱ ላይ የሚያጠነጥን 'አልጸጸትም' የተሰኘውን መጽሐፍ ታህሳስ 10/ 2017 ዓ.ም በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ያስመርቃል። ጃዋር መሃመድ በአገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ፣ በቀጣይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ስለሚኖረው ሚና፣ አገሪቱ ስላለችበት ሁኔታ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ቆይታ አድርጓል።