የትንሳዔ በዓል አከባበር በዓለም ዙርያ በምስል

የፎቶው ባለመብት, Mahibere Kidusan
የምስሉ መግለጫ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በቤተ ክርስትያን የፋሲካን በዓል ለማክበር የመጡ ምዕመናንን ሲባርኩየንባብ ጊዜ: 2 ደቂቃ
ዛሬ ሚየዝያ 12/ 2017 ዓ.ም. በመላው ዓለም የሚገኙ ክርስቲያኖች የትንሳኤ በዓልን እያከበሩ ነው።
በዚህ ዓመት ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች፣ካቶሊኮች እና የወንጌላውያን አማኞች በሙሉ በተመሳሳይ ቀን በዓሉን እያከበሩ ነው።
አብያተ ክርስቲያናቱ የተለያዩ የቀን መቁጠሪያዎችን ስለሚጠቀሙ ይህ ብዙ ጊዜ የሚሆን አይደለም።
በግሪክ ሰማዩ በርችት ሲደምቅ፣ በኢየሩሳሌም ምዕመናን ኢየሱስ ተሰቅሎ ተቀበረ በተባለበት ስፍራ ሻማ አብርተዋል።
የተለያዩ የዓለም አገራት በዓሉን እንዴት እያከበሩ እንደሆነ በምስል ይመልከቱ!

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የምስሉ መግለጫ, ፍልስጤማውያን ክርስትያኖች ኢየሱስ ተሰቅሎ ተቀብሯል ተብሎ በሚታመንት፣ ጥንታዊቷ ኢየሩሳሌም ከተማ፣ በዓሉን ሲያከብሩ
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የምስሉ መግለጫ, በዩክሬን ሌቪቭ ከተማ ምዕመናን የፋሲካ ኬካቸውን የያዘው ዘንቢል እስኪባረክ ድረስ ተሰልፈው ሲጠብቁ
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የምስሉ መግለጫ, በኬንያ ዋና መዲና የሌጊዮ ማሪያ ቤተክርስትያን ምዕመናን የፋሲካ ምሽትን ሻማ በማብራት አክብረዋል
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የምስሉ መግለጫ, የቱርክ ክርስትያኖች በግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ተሰባስበው የፋሲካ እሁድ ምሽት አግለግሎትን ሲካፈሉ
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የምስሉ መግለጫ, በስሪላንካ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስትያን ምዕመናን ጳጳሱ በተገኙበት ቅዳሜ ዕለት የፋሲካ በዓልን ሲያከብሩ
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የምስሉ መግለጫ, በዌስት ባንክ ኢየሱስ ተወልዷል ተብሎ በሚታመንበት ቤተልሔም የኦርቶዶክስ ክርስትያኖች በቤተክርስትያን ተሰባስበው የፋሲካ በዓልን ሲያከብሩ
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የምስሉ መግለጫ, በሩሲያ የቅዱስ ፒተርስበርግ የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ካህን የፋሲካ በዓልን ለማክበር በቤተክርስትያን ለተገኙ ምዕመናን የፋሲካ ኬኮችን እና እንቁላሎችን ከመባረኩ በፊት እየጸለየ