በእሳት የጋየው የጃፓን አውሮፕላን እና ርዕደ መሬቱ የፈጠረው ቀውስ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, የነፍስ አድን ሠራተኞች
በእሳት የጋየው የጃፓን አውሮፕላን እና ርዕደ መሬቱ የፈጠረው ቀውስ

የጃፓን አውሮፕላን ቶክዮ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከሌላ አውሮፕላን ጋር ተጋጭቶ በእሳት ጋይቷል። በውስጥ የነበሩ 400 የሚጠጉ ሰዎች ቢተርፉም ከሌላኛው አውሮፕላን ግን አምስት ሰዎች ሞተዋል። ሁለተኛው አውሮፕላን በርዕደ መሬቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ዕርዳታ ለማድረስ እየተሰናዳ የነበረ ነው። በጃፓን የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ 48 ሰዎች ሲሞቱ በርካታ መሰረተ ልማቶች ወድመዋል።