"እርግዝናዬ ሦሰት ጊዜ የተጨናገፈበትን ምክንያት ለማወቅ ቻልኩ"
ሎይስ ንያጎል በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሦስት እርግዝናዎቿ ተጨናግፈውባታል። ይህንን ውርጃ ያስከተለባት ብላይትድ ኦቩም የተባለ ችግር መሆኑን ባለሙያዎች ነግረዋታል።
በእንዲህ አይነቱ ችግር የሚገጥማቸው ሴቶች ብዙ ጊዜ ከስምንት እስከ 13ኛ ሳምንት ባለው ጊዜ ውስጥ ውርጃ ያጋጥማቸዋል። በእዚህ ሁኔታ ሦስት ጊዜ ወልዳ ለመሳም ያልቻለችው ሎይስ ወደፊት ይሳካ ይሆናል ብላ በተስፋ እየጠበቀች ነው።
ሎይስ ስለገጠማት ችግርና የሕይወት ገጠመኟን ለቢቢሲ አጋርታለች።