ከ12 ዓመታት እስርና ሰቆቃ በኋላ ተስፋ አልቆርጥም የሚለው ከፍያለው
ከፍ ያለው ተፈራ ለ12 ዓመታት እስራት በአስር ላይ ከመቆየቱ በተጨማሪ ሁለት እግሮቹን እንዲያጣ ያደረገው ሰቆቃ ተፈጽሞበታል።
ነገር ግን በህይወት ተስፋ እንደማይቆርጥ በመግለጽ "ተስፋ መቁረጥ የለብንም። ተስፋ መቁረጥ በቁም መሞት ማለት ነው" ይላል።
ተስፋ የቆረጠ ሰው ህይወቱ አልፎ አልተቀበረም እንጂ ሞቷል" ሲልም አክሏል።