በቤይሩቱ ፍንዳታ ባሏን አጥታ ፍትሕ እየጠበቀች ያለችው ሚስት
በቤይሩቱ ፍንዳታ ባሏን አጥታ ፍትሕ እየጠበቀች ያለችው ሚስት
ሐምሌ 28/2012 ዓ.ም. ሊባኖስ ቤይሩት ወደብ ላይ ያጋጠመው ከባድ ፍንዳታ በአካባቢው ያለው የዋና ከተማዋን ክፍል ሙሉ ለሙሉ አውድሞ ከ200 በላይ ሰዎችን ገድሏል።
ከሟቾቹ መካከል የታኒያ ባለቤት የሆነው ፍሬዲ አንዱ ሲሆን፣ ታኒያ ስለ ባሏ ሞት፣ አስካሁንም ፍትሕ ስላለማግኘቷ እና ለወደፊት ተስፋ ስለምታደርገው ለቢቢሲ ተናግራለች።
ፍንዳታው በቤይሩት ወደብ ላይ ለዓመታት በተገቢው ጥንቃቄ ያልተከማቸ የማዳበሪያ መስሪያ ንጥረ ነገር ያስከተለው ሲሆን፣ ከሞቱት በተጨማሪ ቢያንስ 6,500 ሰዎች ጉዳት ሲደርስባቸው፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ቤት አልባ ሆነዋል።
The ከአደጋው ጋር በተያያዘ ባለፉት ሦስት ዓመታት እየተካሄደ ያለው ምርመራ አዝጋሚ ከመሆኑ በተጨማሪ፣ የተለያዩ ሕጋዊ እንቅፋቶች አጋጥመውታል።
ታኒያም ምርመራው አብቅቶ ለሁለት ልጆቿ አባት ሞት ፍትሕን አገኛለው ብላ ተስፋ ታደርጋለች።



