ሰውነትን እንዲህ እጥፍጥፍ በማድረግ ማዘዝ ይቻላል? እንዴት?
ሰውነትን እንዲህ እጥፍጥፍ በማድረግ ማዘዝ ይቻላል? እንዴት?
ጆሬስ ኮምቢላ ይባላል። በሰባት ዓመቱ የሞከረው ሰውነትን የማጣጠፍ ልምምድ በብዙዎች ዘንድ ተዓምረኛ አስብሎታል። ሁሉንም የሰውነት ክፍሎቹን በተለያየ ሁኔታ በማጠፍ ግርምትን የሚፈጥር ትዕይንት ያሳያል።
ይህ ትርዒት ደግሞ በማኅበራዊ ሚዲያ እና በቴሌቪዥን ላይ በማቅረብ ተቀባይነት ከማግኘቱ በፊት፣ ብዙ ችግሮች አጋጥመውታል። ሰዎች አስማተኛ እያሉ ያገሉት እና ይዘባበቱበት እንደነበር ጋቦናዊው ጆሬስ ይናገራል።
አሁን የመተጣጠፍ ችሎታውን በማሳየት ኑሮውን እየመራ ሲሆን፣ በመላው ዓለም እየዞረ ትዕይንት ማሳየት ሕልም አለው።



