አግሯን በአደጋ ያጣችው ሞዴል ወደ መደበኛ የሕይወት እንቅስቃሴ የመመለስ ትግል

አግሯን በአደጋ ያጣችው ሞዴል ወደ መደበኛ የሕይወት እንቅስቃሴ የመመለስ ትግል

ይህች ሞዴል ሲያን ግሪን ትባላለች። የ32 ዓመት ወጣት ስትሆን የአነቃቂ ንግግር አቅራቢ እና ሞዴል ነች።

በአደጋ ምክንያት ግራ እግሯን አጥታለች። የእግሯ መቆረጥ ግን ያሰበችውን ከማድረግ አላገዳትም። እግሯ ከተቆረጠ በኋላ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለመጀመር ወደ ስፖርት ቤት አምርታለች።

በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሰዎች ምን ሊሉኝ ይችላሉ በሚል መጀመሪያ ላይ ፍርሃት ተሰምቷት ነበረ። አሁን ያለምንም ረዳት ስፖርት ቤት ውስጥ እንቅስቃሴዋን እያከናወነች ነው።