እስራኤል በተቃውሞ ስትታመስ የሰነበተችው ለምንድን ነው?
እስራኤል በተቃውሞ ስትታመስ የሰነበተችው ለምንድን ነው?
እስራኤላውያን የአገሪቱ መንግሥት ያረቀቀውን አዲስ የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያን በመቃወም ሳምንታትን አስቆጥረዋል።
ተቃዋሚዎች በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች በአስር ሺዎች አደባባይ ወጥተው ተቃውሟቸውን ቢያሰሙም ፓርላማው ግን ከቀናት በፊት የቀረበለትን የማሻሻያ ረቂቅ ሕግ በመጀመሪያው ሂደት አጽድቆታል።
ተቃዋሚ እስራኤላውያን አዲሱ የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ የፍርድ ቤቶችን ሥልጣን ይጋፋል ቢሉም፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ግን ማሻሻያው አስፈላጊ ነው ብለዋል።



