‘አልተማሩም’ በተባሉ ሴቶች የቋቋመው ስኬታማው የሴቶች ባንክ

‘አልተማሩም’ በተባሉ ሴቶች የቋቋመው ስኬታማው የሴቶች ባንክ

በሕንድ የመጀመሪያው ለሴቶች አገልግሎት የሚሰጠው የኅብረት ሥራ ባንክ በሴቶች ተመሰረተው ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት ነበር።

ነገር ግን ሴቶቹ የባንክ ሥራውን ለመጀመር በቀላሉ አልነበረም ፈቃድ ያገኙት፤ የሕንድ ማዕከላዊ ባንክ መጀመሪያ ላይ ሴቶቹ የተማሩ ስላልነበሩ የፈቃድ ማመልከቻቸውን ሳይቀበለው ቀርቶ ነበር።

ቢሆንም ይህ ሁኔታ የባንኩን ፕሬዝዳንት ከዓላማቸው አላስቆማቸውም ነበር። በዚህም እነሆ አሁን ባንኩ ሴቶችን እያገለገለ 25 ዓመታት አስቆጥሯል።