በሞግዚቷ ተሰርቃ የነበረችው ልጅ ከ51 ዓመታት በኋላ እንዴት ከወላጆቿ ጋር ተገናኘች?

በሞግዚቷ ተሰርቃ የነበረችው ልጅ ከ51 ዓመታት በኋላ እንዴት ከወላጆቿ ጋር ተገናኘች?

በሞግዚቷ የተሰረቀችው ሜሊሳ ሃይስሚዝ በዘረ መል ምርመራ እገዛ ከ51 ዓመታት በኋላ ከቤተሰቦቿ ጋር ስትገናኝ በእንባ ተራጭተዋል። ከአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት ስትሰረቅ ሜሊሳ የ22 ወራት ሕጻን ነበረች። ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ ስትመለስ እናት እና አባቷን በሕይወት ማግኘት ችላለች።