በኳታር የዓለም ዋንጫ ከጨዋታው ቀድመው ሌሎች ጉዳዮች ለምን አነጋጋሪ ሆኑ?

በኳታር የዓለም ዋንጫ ከጨዋታው ቀድመው ሌሎች ጉዳዮች ለምን አነጋጋሪ ሆኑ?

የኳታሩ የዓለም ዋንጫ በጉጉት እየተጠበቀ ነው። ነገር ግን አገሪቱ ባላት የመብት አያያዝ ዙሪያ በርካታ ወቀሳ እና ተቃውሞ እየቀረበባት ነው። ይህም በውድድሩ ላይ ጥላውን ሊያጠላበት ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል።

የውጭ አገር የጉልበት ሠራተኞች አያያዝ ጉዳይ፣ የመናገር መብትን እና አገሪቱ ከተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን አንጻር ያላት አቋም ኳታርን እያስወቀሱ ከሚገኙ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ።