በኳታር የዓለም ዋንጫ ተጫዋቾች እና ተመልካቾች እንዳያደርጉ የተከለከሉት ነገሮች የትኞቹ ናቸው?

በኳታር የዓለም ዋንጫ ተጫዋቾች እና ተመልካቾች እንዳያደርጉ የተከለከሉት ነገሮች የትኞቹ ናቸው?

እየተካሄደ ያለው የኳታር የዓለም ዋንጫ ውድድር በርካታ ድንቅ ነገሮች እየታዩበት ከመሆኑ በተጨማሪ ውዝግቦችንም እያስተናገደ ነው።

ኳታር በባሕረ ሰላጤረው በረሃ ውስጥ አጀብ ያሰኙ ስታዲየሞችን ገንብታ በአረቡ ዓለም የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫ በማስተናገድ ታሪክ አስመዝግባለች።

በተጫማሪም ይህ የዓለም ዋንጫ ከቀደሙት በተለየ በርካታ ትችቶች የተሰነዘሩበት ነው። ኳታር ከእምነት እና ከሕጓ አንጻር የተለያዩ ክልከላዎችን የጣለች ሲሆን፣ በዚህም ሳቢያ ድጋፍ እና ውግዘት ከተለያዩ ወገኖች እየተሰነዘሩባት ነው።

ታዲያ በዚህ የዓለም ዋንጫ ደጋፊዎች እና ተጫዋቾች ፈጽሞ እንዳያደርጉት የተከለከሉት ነገሮች የትኞቹ ናቸው?