መካከለኛው ምሥራቅን ያጥለቀለቀው አደንዛዥ ዕፅ እና የሶሪያ የጦር መሪዎች
መካከለኛው ምሥራቅን ያጥለቀለቀው አደንዛዥ ዕፅ እና የሶሪያ የጦር መሪዎች
ካፕታጎን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መካከለኛው ምሥራቅን እያጥለቀለቀ የሚገኝ አደንዛዥ ዕፅ ነው። የዚህ ዕፅ ምርት እና ዝውውር ከአስር ዓመታት በላይ በጦርነት ስትታመስ ከቆየችው ሶሪያ የሚነሳ መሆኑ ተደርሶበታል።
የቢቢሲ አረብኛ ከሌሎች የምርመራ ጋዜጠኞች ጋር ባደረገው ምርመራ፣ ይህንን ዕፅ የሚያዘዋውሩት ከሶሪያው ፕሬዝዳንት የጦር ሹማምንት ጋራ ግንኙነት ያላቸው መሆናቸውን ደርሶበታል።
በተደረገው ጥልቅ ምርመራም የሶሪያ ምጣኔ ሃብት በዚህ የቢሊዮን ዶላሮች አደገኛ ዕፅ ዝውውር እንደሚደገፍ የሚያመለክቱ መረጃዎች ተገኝተዋል።



