‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች
‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች
እነዚህ የፍልስጥኤማውያን ቤተሰቦች አርብ ዕለት በጋዛ ትልቁ ሆስፒታል ከተፈጸመው ጥቃት አምስት ደቂቃ ቀደም ብለው ነው ከሆስፒታሉ የወጡት። የፍልስጥኤም ባለስልጣናት ጥቃቱን የፈጸመችው እስራኤል ናት ብለዋል። የነዳጅ አቅርቦት በመቋረጡ ብዙ ሕሙማን አደጋ ላይ መሆናቸውን የሆስፒታሉ ሐኪሞች አረጋግጠዋል። እስራኤል ደግሞ ሕጻናቱን ወደ ሌላ ሆስፒታል አዘዋውራቸዋለሁ ብትልም ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥባለች።