ሕይወት በጋዛ፡ "ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል"
ሕይወት በጋዛ፡ "ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል"
በእስራኤል እና ሐማስ ጦርነት ሳቢያ ከቤታቸው ተፈናቅለው ወደ ደቡባዊ ጋዛ እንዲሸሹ የተገደዱ ፍልስጤማውያን “ጦርነቱ 100 ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል” ይላሉ። ባረፉበት የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ፣ ነዳጅም ሆነ መብራት አያገኙም። ምግብ ለማብሰል የሚጠቀሙት ደረቅ እንጨት ፈላልገው ነው። ከ40 ቤተሰቡ ጋር የተሰደደው የጋዛ ነዋሪ ኑሮው ፈታኝ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግሯል።