ሚስቶቻቸውን በቤት ውስጥ ሥራ ለማገዝ ሥልጠና የሚወስዱት ወንዶች
ሚስቶቻቸውን በቤት ውስጥ ሥራ ለማገዝ ሥልጠና የሚወስዱት ወንዶች
ሴቶች በቤት ውስጥ ያለባቸውን የሥራ ጫና ለመቀነስ በኡጋንዳ ያለ አንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ወንዶች ሚስቶቻቸውን በቤት ውስጥ ሥራ እንዲያግዙ ሥልጠና እየሰጠ ነው።
ሥልጠናው በተለይ ልጆችን በማጠብ፣ ምግብ በማብሰል ውሃ በመቅዳት እና የቤት እና የአካባቢ ንጽህናን እንዲጠብቁ ወንዶችን የሚያበረታታ ነው።
ይህ ሲሆንም ሚስቶች ሌሎች ሥራዎችን ለመሥራት እና ለመማር ዕድል ይፈጠርላቸዋል የሚል ሃሳብ አለ።