ከ10 ዓመት በፊት የተቀጣጠለው የግብጹ ጣህሪር አደባባይ አብዮት ምን ፈየደ?
የግብጽ አብዮት ከተጀመረ አስር ዓመት አልፎታል። በፈረንጆቹ 2011 የተጀመረው የግብጽ አብዮት በርካታ ግብጻውያንን አደባባይ አውጥቶ ነበር።
በ18 ቀን የጎዳና ላይ ተቃውሞም ለ30 ዓመታት በስልጣን ላይ የነበሩትን የወቅቱን ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክን ከስልጣን አባሯል። እርሳቸውን የተኩት ሞሐመድ ሙርሲም ብዙም ሳይቆዩ ተመሳሳይ እጣ ፈንታ ገጥሟቸው ከስልጣን ተባርረዋል።
በወቅቱ ብዙ የዴሞክራሲ እና የምጣኔ ሃብት ጥያቄዎች ተነስተዋል።
ታዲያ ከ10 ዓመት በኋላ እነዚያ የግብጽ ሕዝብ ጥያቄዎች ከምን ደረጃ ደረሱ?